Ongoing Contest
የ ኮንተንት ክሬሽን ውድድር
Sewasew Multimedia
በ ኮንተንት ክሬሽን ውድድር እስከ 30,000 ብር ተሸላሚ ይሁኑ! ይህ ውድድር የእጅ ስልካችሁን ተጠቅማችሁ ከ 2 ደቂቃ ያልበለጠ እና ቀለል ያለ የሰዋሰው አፕን የሚያስተዋወቅ ቪድዮ በመስራት እስከ 30,000 ብር ተሸላሚ የምትሆኑበት ውድድር ሲሆን፤ በውድድሩ ለይ አዝናኝ እና ሳቢ ይዘት ያለው የማስታወቅያ ኮንቴንት የሰሩ ተሳታፊዎች አሸናፊ ይሆናሉ። ከብር ሽልማት በተጨማሪ ለሁሉም ተሳታፊዎች የተሳትፎ ሰርተፍኬት እንዲሁም ከ 1 እስከ 3 ላጠናቀቁ በየደረጃቸው የብር ሽልማት እና የእውቅና ሰርተፍኬት ይበረከታል። በዚ ቻሌንጅ አሸናፊ ለመሆን ከናንተ የሚጠበቀው የሰራችሁትን አጭር የማስታወቅያ ቪድዮ ቅኝት ዌብሳይት ለይ በመላክ ሰዎች የእናንተን ቪዲዮ ቮት እንዲያደርጉ ማድረግ ብቻ ነው። ለዚ ቻሌንጅ እንዴት ቪድዮዋችሁን ማዘጋጀት እንደምትችሉ የበለጠ ለማወቅ ከላይ የተቀመጠውን ኢንስትራክሽን ቪድዬ መመልከት ትችላላችሁ። በተጨማሪ ስለውድድሩ ደንብ እና ግዴታዎች ከውድድሩ ጋይድላይን ላይ ያንብቡ። ሌሎች ቻሌንጆችን የሚመለከቱ መረጃዎች ለማግኘት የቲክቶክ ቻናላችንን ይከተሉ።
ይህ ውድድር እስከሚጀምርበት ቀን ድረስ ተወዳዳሪዎች ከ 2 ደቂቃ ያልበለጠ ለተመልካች ሳቢ እና ማራኪ ይዘት ያለው የሰዋሰው App ማስታወቂያ ቪድዮ እንዴት በስልካቸው ማዘጋጀት እንደሚችሉ መለማመድ ይኖርባቸዋል። ለውድድሩ የሚያስፈልጉ መገልገያዎችን እንደ እጅ ስልክ፣ እንደሁም ለሎች ቪድዮውን ለማዘጋጀት የሚጠቅሙ ነገሮችን ማሟላት የኖርባቸዋል።
File Type
Description
ዲስክሪፕሽን:ተጨማሪ ስለ ሰራችሁት ቪድዮ አጭር ዲስክሪፕሽን
የቪድዮ ርዝመት:እስከ 2 ደቂቃ
የቪድዮ ቡዛት:1
የ ቪድዮ መጠን:እስከ 500 MB